በወሎ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የአማራ ዩኒቨርሲቲዎች የጸረ- ኤች አይ ቪ ኤድስ ፎረም የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ።
  February 17, 2019    News

በአማራ ክልል ጤና ቢሮ አጋዥነት የተመሰረተው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጸረ- ኤች አይ ቪ ኤድስ ፎረም በክልሉ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች በኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ በቂ ግንዛቤ ኑሯቸው ራሳቸውን ከበሽታው እንድከላከሉ በትኩረት ይሰራል። በዚህ ፎረም አስሩም በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የባለፉትን ስድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማቅረብ ርስ በርሳቸው በመማማር በቀጣይ በሚሰሯቸው ተግባራቶች ላይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል። በፎረሙ በቀጣይ በትኩረት እንድሰሩ በአቅጣጫና በመልካም ተሞክሮ ከተያዙት ስራዎች መካከል ወሎ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ- ጾታን በሥርዓተ ትምህርት ተቀርጾ በኮርስ መሰጠቱ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መስፋት ያለበት ተግባር ተደርጎ ተወስዷል። በፎረሙ ተገኝተው የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት በወሎ ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ ጾታ ልዩ ፍላጎትና ኤች አይ ቪ ኤድስ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሮዛ ስዩም በሁለት ቀን ቆይታ አንዱ ዩኒቨርሲቲ ከሌላው ዩኒቨርሲቲ አዳዲስ አሰራሮችንና መልካም ተሞክሮዎችን መለዋወጥ የተቻለበት በመሆኑ ፎረሙን በማጠናከር ሁሉንም ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ተመሳሳይ አሰራር በማምጣት ስኬታማ ስራዎችን መስራት እንደሚችሉ ተናግረዋል። በቀጣይ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ፎረም ለማዘጋጀት ሀላፊነቱን ወስዷል።