ሀገር አቀፍ የሰላም፥ የልማትና ብሄራዊ የዜግነት ግንባታ ኮንፍረንስ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ።
  February 17, 2019    News

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ቤት ከFRIEDRICH EBERT STIFTUNG አለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በሀገራችን ሰላም ልማትና ሀገራዊ የዜግነት ግንባታ ተጠናክሮ እንድቀጥል የሚያስችል ሀገራዊ ኮንፍረንስ አዘጋጅተዋል። በዚህ ሀገራዊ ኮንፍረንስ ታዋቂ ምሁራን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የመንግስት ባለስልጣናት ተሳታፊ ሁነዋል። ኮንፍረንሱን በንግግር የከፈቱት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አባተ ጌታሁን በወሎ ህዝብ ውስጥ ለዘመናት ያለውን አንድነትና አብሮ በሰላም የመኖር እሴት ለማስቀጠል ዩኒቨርሲቲው የህዝቡን መልካም እሴቶች የሚያጎሉ የሰላም ኮንፍረንሶችን ሲያካሄድ የነበር ሲሆን ዛሬም ይህንኑ ሰላማችንን የሚያስቀጥል ኮንፈረንስ በማካሄድ የዜግነት ግደታችንን ለመወጣት እንሰራለን ብለዋል። አያይዘውም ፕሬዚዳንቱ ሰላም በእጃችን ያለ ከማንም የማንጠብቀው ሲሆን ከእጃችን ከወጣ ግን ዋጋ የሚያስከፍለን በመሆኑ ሁላችንም የሰላም አምባሳደሮች ሁነን የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል ከራሳችን ልንጀምር ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል። ከፕሬዚዳንቱ ንግግር በኋላ ቁልፍ መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ የኢትዮጵያን ታሪክ ከአጼ ቴወድሮስ የሀገር በእጀ ስልጣንን ጠቅልሎ የመያዝ እሳቤ እስከ ዘመነ ኢህአዴግ የሀገር በወንዜ የዘመድ አዝማድ የስልጣን ትስስር በኢትዮጵያውያን ላይ ያሳረፈውን የመብት ጭፍለቃብ ትዝዝቭታዝው አስቀምጠዋል። ፍ እኩል ሊዳኝ የሚችል ህግና የህግ የበላይነት እንድኖረን ልንሰራ ይገባናል ብለዋል። በዚህ ኮንፈረንስ ለሀገር ፖሊሲ አውጭዎች ግብአት የሚሆኑ ጥናቶች በምሁራን ቀርበው ተሳታፊዎች በቀረቡት ጥናቶች ላይ አስተያየቶችን በመስጠትና ጥያቄዎችን በማቅረብ ውይይት ተካሄዶባቸዋል ። በመጨረሻም ኮንፈረንሱን አስመልክተው የወሎ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ጌታቸው ........ በኮንፈረንሱ ጥናት አቅራቢዎችንና ተሳታፊዎች ላቀረቧቸው ጥናቶችና ለሰጧቸው ገንቢ አስተያየቶች ምስጋና በማቅረብ ኮንፍረንሱ ተጠናቋል።