ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ ከመጡ የሲቪክ ማህበራት ጋር ውይይት አደረገ
  February 17, 2019    News

ኢትዮጵያዊነት ተቋም" የዜግነት ግንባታ በማለት በአሜሪካን ሀገር ባሉ ኢትዮጵያዊ የተመሰረተው የሲቪክ ማህበር በሀገራችን ያለው ብሄር ተኮር ፖለቲካ የሀገርን ህልውና እየተፈታተነ መምጣቱን ተከትሎ ከባድ ቀውስ ከማስከተሉ በፊት የዜግነት ግንባታ ለማካሄድ በሚል ዓላማ ተቋቁሟል። ይህ የሲቨክ ማህበር ይህንን ዓላማ ለማሳካት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ውይይት አካሄዷል። ማህበሩ የተመሰረተበትን ዓላም ለዩኒቨርሲቲው ምሁራን በማቅረብ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን ከምሁራን ተቀብሏል። በዚህም ውይይት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ሲቪክ ማህበሩ ይዞት የተነሳው ሀሳብ መልካም መሆኑን በመጥቀስ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የማህበሩ የዜግነት ግንባታ ተግባር መዳሰስ እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አያይዘውም ምሁራኑ ሲቪክ ማህበሩ በአማራ ክልል ተንጠልጥሎ እንዳይቀር ሁሉንም የኢትዮጵያ ክፍሎች ባማከለ መልኩ ሊታይ ይገባዋል ብለዋል። የሲቪክ ማህበሩ በአማራ ክልል በሚገኙ የከፈተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ተመሳሳይ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በቀጣይም ከአምቦና ከአዳማ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ውይይት ለማድረግ እቅድ እንደያዘ ከማህበሩ ሊቀ-መንበር የተሰጠው መግለጫ አስታውቋል።